ኦርቶዶክሳውያንና ቅድስት ቤተክርስትያን ዘመኑን የሚመጥን ኣዲስ ትይዩ ማህበረሰብ መገንባት ኣለባቸው

የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ላይ ብልጥግና የከፈተው ጦርነት ወደ ኣሰቃቂ የርስበርስ ጦርነት ካልተሸጋገረና በኣጭሩ የሚቋጭ ከሆነ ተመሳሳይ ችግር ተመልሶ እንዳይመጣ የሚያስችል ጠንካራ ኣቅም ለመመስረት ኦርቶዶክሳውያንና ቅድስት ቤተክርስትያን ዘመኑን የሚመጥን ኣዲስ ትይዩ ማህበረሰብ ለመገንባት መነሳት ኣለባቸው።


ከ አጼ ኃይለስላሴ ካቶሊካዊ ኣውሮፓዊ ዘመናዊነት (modernization and centralization project) በፊት ቤተክርስትያን በገዥዎች የምትፈራ ራሷን የቻለች ተቋምና ትይዩ ማህበረሰብ የነበራት a state within a state ነበረች።

ትይዩ ማህበረሰብ ማለት ከኣለማዊው መንግስት ትይዩ የሆነ የኦርቶዶክሳውያንን ጥቅምና እሴት የሚያስጠብቅ ራሱን የቻለ ማህበረሰብ ማለት ነው። ይህም የኦርቶዶክስ ባንክ የኦርቶዶክስ ትምህርት ቤት ከመዋለ ህጻናት እስከ ዩኒቨርስቲዎች የኦርቶዶክስ የህግ ጥብቅና ተቋማት የኦርቶዶክስ የፖሊሲና የምርምር ተቋማት (Think tanks) የኦርቶዶክስ የ ዕርዳታ ድርጅቶችና NGOs መቋቋም ኣለባቸው።

በርግጥ ሁሉንም በዕኩልነት የሚያገለግል መንግስት ቢኖር ይህን ማድረግ ባላስፈለገ ሆኖም ዘመናዊ መንግስታት ኣካታች ለመምሰል በሞሞከር የጥቂቶችን ኣጀንዳና ፋሺዝም (Minority fascism over majority) በብዙሃን ላይ ለመጫን የሚሞክሩ ሆነዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ኦርቶዶክሱን ላለፉት ስድሳ ኣመታት ከወደቁ ነገስታት ጋር እኩል በማመሳሰል የጭፍጨፋ ሰለባ ያደረጉ ኣናሳ ኧክራሪና ዘረኛ የግራ ፖለቲካ ኃይሎች መግስታዊ ስልጣንን ተቆጣጥረዋል። ባለፈው ኣራት ኣመት ደግሞ ብልጥግና የሺሻ ወንጌል የደነዘዘ ለራሱም ለማንም የማይሆን ኣደገኛ ኃይል ስልጣን ላይ ወቶ በየጊዜው የኦርዶክሱን ደም በደቡቡ የኣገሪቱ ክፍል እያፈሰሰ ይገኛል።

በመሆኑም ቅድስት ቤተክርስትያን ጥንታዊ ማንነትዋን ፈልጋ በማግኘት መንግስትና ኣለማዊውን ማህበረሰብ የሚገዳደር ራሱን የቻለ ትይዩ ማህበረሰብ በቅዱስ ሲኖዶስ መሪነትና በጠቅላይ ቤተክህነት ኣስፈጻሚነት መመስረት ኣለባት። ዘመኑ ተቀይሯል ፤ የቀድሞዋ ለይስሙላው ቢሆን ክርስትያን የምትባለዋ ኢትዮጵያ ዛሬ የለችም። ቤተክርስትያን ከጊዜው ጋር የሚሄድ ኣስተዳደር ካላቆመች ዘመኑ ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ከሰሞኑ ክስተት የበለጠ ኣስተማሪ የለም ፥

ህዝቤ ካለማወቅ ጠፋ እንዳለው በኋላ ቀሩ መዋቅር የትም እንደማይደረስ ሊታወቅ ይገባል። ቤተክህነቱን በገዛ ቄሶቹ ጭምር የማይታመን የማፍያ ተቋም ያደረገው በኣጼ ኃይለስላሴ ዘመን የተጀመረው ካቶሊክ ኣውሮፓዊ ዘመናዊነትና ማዕከላዊነት ነው ፥ ጀማሪ ፋሽስቱ ኣብይ ኣህመድም እኔም እንዳለፉት ገዥዎች ቅዱስ ሲኖዶስና ቤተክህነቱን ካልተቆጣጠርኩት በሚል ዕብሪት ነው የሰሞኑን ጦርነት የከፈተው። ከ አጼ ኃይለስላሴ ካቶሊካዊ ኣውሮፓዊ ዘመናዊነት በፊት ቤተክርስትያን በገዥዎች የምትፈራ ራሷን የቻለች ተቋምና ትይዩ ማህበረሰብ የነበራት a state within a state ነበረች። ያንን ማንነቷን ካልመለሰች ታሪክ ብቻ የምትሆንበት ግዜ ቅርብ ነው።

Post a Comment

Previous Post Next Post