ጥበቡ ወርቅዬ ወደ ሙዚቃው አለም ሊመለስ ነው!

 በ 1990ዎቹ አጋማሽ በለቀቀው አልበም የሙዚቃውን ኢንደስትሪው በዝና የተቀላቀለው አርቲስት ጥበቡ ወርቅዬ ሙዚቃ አቁሜያለው ካለ ከአጭር ጊዜ በኋላ ወደ ሙዚቃው ኢንደስትሪ ሊመለስ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ይፋ አድርገዋል።

አርቲስቱ በ1990ዎቹ አጋማሽ ባወጣው የዘላለሜ ነሽ አልበም ከፍተኛ ዝናን አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ከዛ ዘመን በኋላ በተለይም የሸዋንዳኝ ኃይሉ እና ዘሪቱ ከበደ አልበሞች ከወጡ በኋላ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ የመጣው አብዮት ምቾት ካልሰጣቸው በርካታ ምርጥ ድምጻዊያን አንዱ ነበር። ጥበቡ ወርቅዮ ኢንተርቴይንመት በሚልም የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት ከፍቶ ነበር። ሆኖም በሙዚቃው እንደስትሪ ላይ የተፈጠረው ቁልቁል መውረድ እና የቅጅ መብት መጣስ ችግር አርቲስቱን እንዳበሳጨው የቅርብ ምንጮች አወርተዋል። ይባስ ብሎ በቅርቡም ጠቅላለውን ከሙዚቃ አለም መሰናበቱን በአንድ የቴሌቪዥን ሾው ላይ ቀርቦ ተናግሯል ተብሎ ተዘገቧል።



ይሁን እንጂ ሰሞኑን የሸገር ፖስት ሪፖርተር ያናገራቸው የአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች እንደሚሉት ተወዳጁ ድምጻዊ ድንገቴ በሆነ አመላለስ ወደ ሙዚቃው ኢንደስትሪ ይመለሳል። እንዴት እርግጠኛ ሆናቹ ብሎ የሸገርፖስት ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው እነዚሁ የአርቲስቱ የቅርብ ምንጮች እራሱ አርቲስቱ በቅርቡ የመመለሱን ጉዳይ ለቅርብ ሰዎቹ ሲያወራ ተሰምቷል ብለዋል።

ባለፈው ወር ፖሊስ ከኢትዮጵያ ኦዲዮ ቪዡዋል አሳታሚዎች ማህበር እና ከሌሎች ኃይሎች ጋር በመሆን በመላው ኢትዮጵያ በወሰደው ለቀማ በርካታ ሰዎች በቅጅ መብት ጥሰት ተጠርጥረው ታስረዋል።
አሁን እንደድሮው ሞባይል ላይ ሙዚቃ እንጭናለን ብለው በአደባባይ ማስታወቂያ ህገወጥ ስራ ሲሰሩ የኖሩ ሞባይል ቤቶችም አፋቸውን ዘግተዋል። ምናልባት እነዚህ ወቅታዊ ሁኔታዎች የአርቲስቱ አድናቂዎች ካሳዩት መከፋት ጋር ተዳምረው የአርቲስቱን ወደ ሙዚቃው አለም መመለስ እያፋጠኑት ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል። ሸገርፖስተ አርቲስቱን አግኝቶ ለማጣራት ያደገረው ጥረት ስልክ ሊያነሳ ባለመቻሉ ለጊዜው አልተሳካም። እስከመጨረሻው ጥረቱን ይቀጥላል።


 By Shegerpost staff writer 

1 Comments

  1. weshetamoche yemetawrut tefabachehu ende sent neger eyale alu eyalachehu tawralachehu ? asafarwoche

    ReplyDelete
Previous Post Next Post