ብርሃኑንም ኣብይንም ለረጅም ጊዜ የደገፈው ኣማራውና ኦርቶዶክሱ በከባዱ ነው የተከዳው :: ሙሉውን ድምጽ ከዚህ ስር ባለው ሊንክ ገብተው በመስማት የራስዎን ፍርድ ይስጡ!
የብልጥግና መንግስት የትምህርት ሚኒስትር የሆኑት የኢዘማው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሚስጥር ኣፈትልኮ በወጣ የፓርቲያቸው የኣምስት ኣመት ግምገማ ላይ በተለምዶ የኣንድነት ሃይል የሚባለው ቡድን የተዳከመበትና ኢዜማም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነት ያጣበት ምክንያት በስሜት የሚነዱ ያሏቸው ኣካላት ከኦሮቶዶክስና ኣምሃራ ያልተላቀቀች የድሮዋ ኢትዮጵያ ተመልሳ እንደማትመጣ መቀበል ስላቃታቸው ነው ብለዋል።
ሁለት ሰዓት ሙሉ እንደ ጆሴፍ ስታሊን ያለምንም ተናጋሪ ብቻቸውን ኣውርተው ተጨብጭቦላቸው በወረዱበት በዚህ የፓርቲው ግምገማ መድረክ ኢዜማ ከኣማራና ኦርቶዶክስ የፀዳ ኣዲስ መዋቅርና ኣመራር እንደሚያስፈልገውና ይህንንም ለማድረግ ከመጪው ምርጫ በፊት የስድስት ወር ስልጠና ለኣዳዲስ ኣመራሮች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
ዶክተር ብርሃኑ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ፖለቲካው መድረክ ብቅ ያሉት በ ፩፱፱፫ (1993) ዓም በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ በተነሳ ብጥብጥ ወቅት ነበር። በጊዜው ከታዋቂው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ጋር ባደረጉት ንግግር ታዋቂ ሆነው ነበር። ብዙ ሰው የተቀበላቸውም በፕሮፌሰር መስፍን በኩል ነበር። ዶክተር ብርሃኑ ከምርጫ ፱፯ (97) በኋላ ባሳተሙት የነጻነት ጎህ ሲቀድ መጽሃፍ ወያኔዎች "የኛ ሰው ነህ ስንልህ እንዴት ከትምክህተኛው መስፍን ወልደማርያም ጋር ትውላለህ" ብለውኛል ብለው ጽፈው ነበር። ዶክርተር ብርሃኑ ኣሁን ከብልጥግና ጋር የሚያራምዱት ከኣማራና ኦርቶዶክስ የጸዳች ኢትዮጵያ ኣጀንዳ መጀመርያ መቀንቀን የጀመረው በ ወያኔ ህወሃት ነበር።
ዶክርተ ብርሃኑ ነጋም ሆነ ዶክተር ኣብይ ኣህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ኦሮሞ ናቸው እስላም ናቸው ጴንጤ ናቸው ሳይል የደገፋቸው የኣማራውና የኦሮቶዶክስ ማህበረሰብ ነበር። ብርሃኑ ነጋ ያለምንም ውጤት ፩፫ (13) ኣመት የመሩት ግንቦት ሰባትም ሆነ ያሁኑ ኢዜማ ኣብዛኛው ኣባልና ደጋፊው ወይ ኣማራ ወይ ኦርቶዶክስ ነው። ብርሃኑ ነጋ በዚህ ኣካሄድ ለኣብይ ሲሉ ፓርቲውን ሙሉ ለሙሉ ለማፍረስ መወሰናቸውን ታዛቢዎች ይናገራሉ።
በሚስጥር በተለቀቀው ግምገማ ላይ ዶክተር ብርሃኑ ኣምስት ኣመት ሙሉ በኣረመኔነትና ለሰው ህይወት ግዴለሽነት ደም እያፈሰሰ ያለውን የብልጥግና ዘረኛና ዘራፊ ቡድን ለኣገር ስጋት ኣይደለም ሲሉ ተከላክለውታል።
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከግንቦት ሰባት መክሸፍ በኋላ ከቀድሞ የድርጅቱ ኣማራ ታጋዮች ጋር በገቡት የግል ቂም ምክንያት ለዘመናት የተከበረ ስብዕናቸውንና የትግል ጓደኞቻቸው የሆኑትን እነ ኣንዳርጋቸው ጽጌ ና ነኣምን ዘለቀን ሙሉ በሙሉ ከድተው በአብይ ዕቅፍ ውስጥ ገብተዋል ነው የሚባለው።
ሙሉውን ድምጽ ከዚህ ስር ባለው ሊንክ ገብተው በመስማት የራስዎን ፍርድ ይስጡ!
https://youtu.be/jYD5Tji9x-A?si=5E0hszwbxx19ZrIR