"ከህወሃት ጦርነት በላይ የከበደን የፋኖ ሽምቅ ውጊያ ነው" ብርሃኑ ጁላ

"ከህወሃት ጦርነት በላይ የከበደን የፋኖ ሽምቅ ውጊያ ነው" ብርሃኑ ጁላ::






የቀድሞው የኢሃዴግ ሰራዊት በርበሬ ሰፋሪ ወይም ሎጅስቲክ ክፍል ሃላፊ የነበረውና የአሁኑ የኣብይ ቅጥረኛ ሰራዊት ሊቀመንበር ብርሃኑ ጁላ የፋኖው ጦርነት ያመጣውን ግፊት ተከትሎ በተደጋጋሚ ቴሌቪዥን ላይ እየቀረበ ይገኛል። 

ሰሞኑን በገዢው ስርዓት ብሄራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀ ኑዛዜው የብልጥግናው መንግስት ከህወሃት ከኦነግና ከፋኖ የገጠመው ጦርነት ተደላድሎ እንዳይገዛ እንዳረገው ገልጾ ከሁሉም ጦርነቶች በላይ የከፋው ግን ከዓማራ ብዙሃን ክፍላተ ሃገሮች የገጠመው የፋኖ የሽምቅ ውጊያ እንደሆነ ተናግሯል። 

ብርሃኑ ሲናገር የህወሃቱ ውጊያ መደበኛ ውጊያ ስለነበር ሁላችንም እኩል ጉዳት ደርሶብናል ፥ የፋኖ ውጊያ ግን የቅጥረኛውን ሰራዊት ቁመና ብቻ እያሽመደመደ በመሆኑ እጅግ ኣስቀያሚ ነው ሲል ነው የገለጸው። 

ቪዲዮውን ይዩት 👇

ብርሃኑ በመግለጫው ሸኔ የሚለውን ሃይል ደጋግሞ ቡድኑ ራሱን በሚጠራበት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት OLA በሚል የጠራው ሲሆን የብልጥግናው መንግስት የሸኔን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ እየተገበረ ቢሆንም ስልጣኑን እኛ ካልያዝነው እያሉ ነው የሚወጉን ሲል ተናግሯል። 

ብርሃኑ በመግለጫው ኦሮምያ በሚባለው ክልል የሚኖሩ ከኣስር ሚሊየን በላይ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ኣንድም ኣይነት ውክልና በክልል ተብዬው ኣስተዳደር ሊኖራቸው ኣይገባም ብሏል።

በዚህ ኑዛዜ ብርሃኑ ጁላ ከትግራዩ ጦርነት በፊት በኣማራ ተብዬው ክልል የተፈጸሙ የታዋቂ ሰዎች ግድያዎችን የብልጥግናው መንግስት እንዳቀነባበረውም ፍንጭ ሰቷል።

ሙሉ ንግ ግሩን የብልጥግናው መንግስት ብሄራዊ ቴሌቭዥን የዩቱብ ገጽ ላይ ገብገው ይመልከቱ።

Post a Comment

Previous Post Next Post