ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ቤቶች ፕሮጀክትን መከታተል ጀመሩ

 በርካታ የመንግሥት ተቋማት የተካተቱበት የአዲስ አበባ ቤቶች ‹‹ኦፕሬሽናል ኮሚቴ›› መቋቋሙን የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ የሚኒስትሩን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጭምር ፕሮጀክቱን መገምገምና መከታተል መጀመራቸውንና በፍጥነት እየተገነባ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሠረት በአዲስ አበባ ለመገንባት የታቀደው 150 ሺሕ ቤቶችን እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ  በ2007 ዓ.ም. የሚጀመሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሳይጨምር ዕቅዱ 'ከመቶ በመቶ በላይ ይሳካል' ብለዋል፡፡ 
‹‹በዕቅድ ዘመኑ የተያዘውን በላቀ ደረጃ ብናሳካም ፍላጐቱን ካለሳካን ትልቅ ፈተና ነው የሚሆነው›› ብለዋል፡፡
በመሆኑም መንግሥት እየተንቀሳቀሰ ያለው በጂቲፒ የተቀመጠውን ለማሳካት ብቻ ሳይሆን የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የቤት ፍላጐት ለማሟላት ነው ብለዋል፡፡
ይህንን ‹‹ኦፕሬሽናል ኮሚቴ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየወሩ መገምገም እንደ ጀመሩ ያስረዱ ሲሆን የከተማ ልማት፣ ቤቶና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ደግሞ በ15 ቀን ይከታተለዋል ብለዋል፡፡
የቤቶች ማስተላለፍና የፋይናንስ ሥራዎችን በተመለከተ በመንግሥት አስተባባሪነት ለሚገነቡ ቤቶች እስከ መጋቢት ወር ድረስ 4.1 ቢሊዮን ብር ቤት ፈላጊዎች መቆጠራቸውን አስረድተዋል፡፡ 
በዚህም መሠረት ከ20/80 ቤት ተመዝጋቢዎች 1.09 ቢሊዮን ብር፣ ከ40/60 ተመዝጋቢዎች 2.69 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከ10/90 ተመዝጋቢዎች 23 ሚሊዮን ብር መቆጠቡን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡
በሁሉም የቤት ፕሮጀክቶች ከዚህ ቀደም የተጀመሩ 95 ሺሕ ቤቶች ግንባታ አፈጻጸም 90 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል፡፡ በ2006 ዓ.ም. 50 ሺሕ ቤቶች ግንባታ የተጀመረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሦስት ሺሕ ቤቶች ግንባታ 30 በመቶ ደረጃ መድረሱን፣ በ10/90 ቤቶች ፕሮግራም የተጀመሩ 24,288 ቤቶች 62.2 በመቶ መድረሱን እንዲሁም በ40/60 የቤቶች ፕሮግራም በ2005 ዓ.ም. የተጀመሩ 1,292 ቤቶች ግንባታ አፈጻጸም 45.3 በመቶ መድረሱንና በዚሁ ፕሮግራም በ2006 ዓ.ም. የተጀመሩ 2,203 ቤቶች ግንባታ 18.07 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል፡፡    
ቤት ፈላጊዎች 4.1 ቢሊዮን ቆጥበዋል
         

Post a Comment

Previous Post Next Post